“ዋገበታ የወንጌል አገልግሎት” በደቡብ ኢትዮጵያ በዶዮገና ወረዳ፣ ዋገበታ በሚባል አካባቢ የሚካሄድ አገልግሎት ነው። “ዋገበታ” ከተፈጥሮው ውበት ባሻገር ስያሜውም አስደነቂ ነው፣ ሥያሜው “ዋዕ ገበተ” ከሚሉ ሁለት የሐዲይኛ ቃላት (“ዋዕ” = የእግዚአብሔር | ገበተ = ማዕድ) የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም “የእግዚአብሔር ገበታ” ማለት ነው። ስያሜው የሚያመለክተውም

ስለማንነታችንን ለመገንዘብ እዚህ ይጫኑ።
ጎድጓዳ ሳህን የሚመስለውን የሸለቆውን ልዩ የተፈጥሮ አቀማመጥ ነው።
የአገልግሎቱ አጠቃላይ ዓላማ ሰዎች ልባቸውና አስተሳሰባቸው ታድሶ ለራሳቸው ለቤተሰባቸውና ለአገራቸውም ጠቃሚ ዜጎች እንዲሆኑ ማገዝ ሲሆን ይህንኑ በማከናወን ረገድ በዋገበታ የምትገኘው የቀጬራ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ተልዕኮዋን እንድትወጣ እናግዛለን።