ማንነታችን

የአገልግሎቱ ዋነኛ ባለቤት በዋገበታ የቀጬራ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ዋነኞቹ ደጋፊዎችዋ ከአብራኳ የወጡት ልጆችዋ ናቸው፣ ከነዚህም መካከል በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩት የቀድሞ አባላትዋ ዋነኞቹ ሲሆኑ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ መስራች አባት የነበሩት የወንጌላዊ ጉራቻ ሕምበጎ ቤተሰብም በእርሳቸው የተጀመረው የወንጌል ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። ከነዚህ በተጨማሪ የአገልግሎቱን ራዕይ ሲሰሙ ልባቸው ተነክቶ አገልግሎቱን በገንዘብም ሆነ በጸሎት ለመደገፍ ቃል የሚገቡ የወንጌል ማኅበረተኞችም አሉ።

ስለአገልግሎቱ ታሪካዊ አጀማመር ለማወቅ እዚህ ይጫኑ።